Sunday, March 9, 2014

የወያኔ የግፍ ኣስተዳደር ውጤት

በኣሁኑ ሰኣት በሀገራችን ላይ በግልጽ የሚታየው የጎሳ እና የዘር መድሎ ውጤት ህውሀት መስራቾች ስልጣን ለመያዝ ብሎም ህዝቡን በመከፋፈል ስልጣንን ለማራዘም ሲመሰረት የተጠነሰሰ ሀሳብ ነው ይህም ዛሬ ሀገራችን ውስጥ ባሉ ከትንሽ አስከትልቅ ተቋማት ላይ በግልጽ እየታየ ነው ። የህዝብ መገልገያ ተቋማት እውቀታቸው ለቦታው በማይመጥን ነገር ግን የወያኔ ታማኝ ኤጀንት ባለስልጣናት መተዳደሩ የአሰራር በለሎኦች አንዲስፋፉ ተቋማትን አንደግል ንብረታቸው በመያዝ ሰራተኞች ላይ የሚፈጠሩ በደሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ አየተስፋፋ በመምጣቱ ዜጎች ተምረው ሀገራቸውንም ሆነ ህዝቡን አንዳያገለግሉ አንቅፋት ሆኖባቸዋል።
ሀገራችን ከፍተኛ የሰው ሀይል ከሚሰደድባቸው ሀገሮች ቀዳሚ ሰንጠረዥ ውስጥ ትገኛለች ከስደተኞቹም ውስጥ አብዛኛው ወጣት እና የተማረው የሰው ሀይል ነው ፣ ኣንዲት ሀገር ካላት መሰረታዊ ሀብቶች ዋነኛው ወጣት የሰው ሀይል ነው። ዛሬ ሀገራችን ባለው ኣስከፊ የኣስተዳደር ችግር ምክኒያት ልጆቿ በስደት መሬቷን በሽያጭ አያጣች ትገኛለች ለዚህም በቅርቡ በኣለማችን ታላላቅ ሚዲያዎች መነጋገሪያ የነበረው ረዳት ፓይለት ሀይለመድን ኣበራ ጉዳይ እንደዋና ምሳሌ ተጠቃሽ ነው ።


                                                                                                    በጀሚ ነሲቡ

No comments:

Post a Comment